Prisons Ministry

የማረሚያ ቤት አገልግሎት

ይህ አገልግሎት ስራ የጀመረው በ2003 (2010) ሲሆን በሃገሪቱ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ለመንቀሳቀስ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ በመውሰድ የሚንቀሳቀስ ነው። ማረሚያ ቤቶቹንም ፕሮግራም በማስያዝ ወደሚገኙበት ስፍራ በመሄድ ከወንጌል ክፍል ጋር በመተባበር ወንጌልን ይሰብካል። የተለያዩ አልባሳትን፣ መጽሐፍትንና ሣሙናና ያደርሳል፡፡ አንዲሁም ማረሚያ ቤቶቹ ባሉበት ከተሞች በጎዳና ላይ ወንጌልን ይሰብካል። በየከተማው በሚገኙ ሆስፒታል ታመው የተኙትን በመጠየቅ፣ በመጸለይ፣ ወንጌልን በመመስከር፣ አስፈላጊ ሲሆን አንዳንድ እርዳታ በማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ማቴ.25፡34-46 ያለውን የጌታችንን ትዕዛዝ የሚያስፈጽም አገልግሎት ነው፡፡
ከዚህ ባሻገር አንዳንድ የማምለኪያ ቦታን ለሚገነቡ ማረሚያ ቤቶች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግና አስፈላጊ በሆነበት ስፍራ የቴሌቪዥንና ዲሽ ገዝቶ በመስጠትና በመሳሰሉት እገዛ አድርጋለች፡፡ በሚቀጥሉት ዓመታት ቤተ ክርስቲያናችን ቢያንስ በአመት እስከ አምስት ማረሚያ ቤቶችን ለመጎብኘት ዕቅድ ይዛለች፡፡ በዚህ አገልግሎት አብራችሁን ለመስራት ሸክም ያላችሁ ወገኖች ከአላችሁ ቤተ ክርስቲያናችን  በሯን ክፍት አድርጋ ትጠብቃችኋለች፡፡ መከሩ ብዙ ነውና! ከአላችሁ ቤተ
ከዚህ ቀደም ቤተ ክርስቲያኗ ከአገለገችባቸው ማረሚያ ቤቶች መካከል፡-

ቀን

ማረሚያ ቤት የዳኑ ሠዎች ቁጥር
16/04/03 አዲስ ዓለ / 27
21/05/03 ወሊሶ   80
1/ 08/ 03 ሆሳዕና 45
22/05/03 ወላይታ 35
26/05/04 ዱራሜ 61
15/07/04 ቡታጅራ 97
13/08/04 አምቦ 111
15/03/05 አዋሳ 300
05/08/05 ፍቼ  417
10/08/05 ሻሸመኔ 222
03/05/06 አዳማ 147
21/10/06 አሰላ 354
23/10/06 አዳማ 200
16/11/08 ሻሸመኔ 202
አጠቃላይ ድምር 2298
2017-05-02T01:00:31+00:00