Freedom Teleconference

የነፃነት የስልክ አግልግሎት የተጀመረው በ2008 (2015) በአሜሪካ በአትላንታ ባለችው ቤ/ክ ሲሆን አላማው ሠዎችን ከተየያዩ ሥፍራዎች ሆነው ስልክን በመጠቀም በአንድ አላማ ማገናኘት ነው። ሲጀመርም የ60 ቀን አመታዊ የጾምና የፀሎት ወቅት ሲሆን በጊዜው እየተገናኝን የምናመልክበት ስፍራን በእየቀኑ መጠቀም ስለማንችል በስልክ እየተገናኝን በእየለቱ በቀን ሶስት ጊዜ ማለትም ጠዋት፣ ምሳ ሰዓት እና ማታ ማታ ላይ እየገባን በህብረት እየፀለይን እና ቃል እየተማርን ቆየን። ይህ መንገድ ደግሞ የ እ/ር ፈቃድ ሆኖ ለሌሎች ብዙ በረከቶች ምክያት ሆነ። በአትላንታ ውስጥ ላሉ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በአሜሪካ እንዲሁም በካናዳ ያሉ ቅዱሳኖች ሁሉ አብረው በዚህ የስልክ አገልግሎት ውስጥ መግባት ቻሉ። እ/ር ለሠጠን የ60 ቀን የጾምና የፀሎት አመታዊ ጊዜ በመሳተፍ አብረውን ያሉ ሁሉ፣ ከእኛ ጋር አንድ ከተማ ላይ ባይኖሩም የዚህ በረከት ተካፋዮች መሆን ቻሉ።

በዚህ መስመር ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ እየገቡ እና እየተባረኩ አሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን ለአብሮ ሠራተኞች የአገልግሎትን በር በመክፈት ቅዱሳን በፀሎት፣ በዝማሬ እና በቃል በማገልገል ሀያላን ሆነው እንዲነሱ እድሎችንም ጭምር ከፍቶአል።ደግሞም ይህ መስመር በተመሳሳይ መልኩ ለአመታዊ 21 ቀን የጾምና የፀሎት ጊዜም ያገለግላል። ከዚህም ባሻገር መጋቢዎቻችን የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት እና እንደአስፈላጊነቱ አብሮ ሠራተኞችን ለማስታጠቅም የምትጠቀመው መሆን ችሎአል። ይህ መስመር ላይ የሚደረጉ ፕሮግራሞች ደግሞ መቀዳት ስለሚችሉ ይህንን በማድረግ ለብዙዎች በረከቱን ማዳረስ እና ደግሞም ለታሪክ (historican data) ማስቀመጥ ተችሎአል።

2017-04-30T05:26:00+00:00