Children, Teens and Youth

የወጣት አገልግሎት

ወጣቱ በወጣትነት ዕድሜው በትምህርትና በሥልጠና ካልተያዘ ምን ያህል ለጥፋት የተጋለጠ እንደሆነ ስለገባን በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ተደራጅተው ከመሰልጠንና የወንጌል ጥናት ከማካሔድ በላይ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን በማሳደግ ወጣቱን ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው በማሰብ ትምህርቱን በእንግሊዘኛ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ወጣቱን በመንፈስ ቅዱስ እሳትና በኃይል ከማስታጠቅ ባሻገር መሪ ማድረግ፣ በመንፈሳዊ እንቅስቃሴ ውሰጥ የለውጥ ሐዋሪያ እንዲሆኑ ማብቃት፣ በትምህርታቸውና በሁለንታዊ ህይወት ላይ ተጽዕኖ ማምጣት የሚችሉ ወጣትን ማፍራት በሚል ግንዛቤ እንሰራለን፡፡

የሚሰጠውን አገግሎቶች በተመለከተ

መንፈሳው መልዕክቶችን ማስተላለፍ፣ ኮንፍረንሶችንና ከሩሴዶችን ስልጠናዎችን ማዘጋጀት፣ የጸምና የጸሎት ፕሮግራሞችን ጊዜያት ማዘጋጀት፡፡ የምክር አገልግሎት መስጠት፣ የአገልግሎት ዕድል በመስጠት ማብቃት ሲሆን በዚህም ምክንያት ወጣቶች በቁጥር እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በየአጥቢያው የወጣት ቤተ ክርስቲያንም ተቋቋሟል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ወጣቶችን የምናያቸው የ1000 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ራዕይ አስፈጻሚ እና የቤተ ክርስቲያን ተካይና መሪዎች አድርገን ነው፡፡ ምክንያቱም ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያን ሲተክል ሰላሳ ዓመት ያልሞላው ወጣት እንደነበርና ቤተ ክርስቲያኑም እጅግ ብዙ ቁጥር ምዕመን እንደነበራት መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል፡፡ የእኛም ወጣት ቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት የራሳቸው አገልግሎት /Department/ እንደ ስነጽሑፍ፣ ኳየር፣ ወንጌል የመሳሰሉትን አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በህጻናት፣ በቲንና፣ በወጣት አደረጃጀታችን በጣም ተጠቃሚ በመሆናችን ቤተ ክርስቲያን ተካይ እየሆኑ የተላኩ ለጌታ ትልቅ ልብ ያላቸውና በመንፈስ እሳት የተቀጣጠሉ ወጣቶችን ማፍራት ችለናል፡፡ ይህንን ያደረገውን አምላካችንን ማመስገንና ማክበር እንወዳለን፡፡ ምስጋናውን ሁሉ ይህንን ያደረገውና የሰራው አምላካችን ክብሩን ሁሉ ጠቅልሎ ይውሰድ! ጌታችን ምንም የማይሳነው አምላክ በመሆኑ ወደፊት ከዚህ የበለጠ እንደሚያሰፋን እርግጠኞች በመሆናችን በዕምነት እንሰራለን፡፡

 

የቲን /Teens/ ቤተ ክርስቲያን

ይህ ክፍል ከአስራ ሶስት እስከ አስራ ስምንት ዓመት የሚሆናቸውን ቲኖችን በቤተ ክርስቲያን ደረጃ በማዋቀር አንድ ቤተ ክርስቲያን ማድረግ ያለባትን ነገሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን ማስተማር፣ ማሰልጠንን፣ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት እንዲሞሉ፣ በዕድሚያቸው ምክንያት የሚገጥሟቸውን ችግሮች መቋቋም እንዲችሉ በአመራር ደረጃ እወቀት ይዘው እንዲያድጉ ትምህርትና ስልጠና መስጠት፣ ወደፊት ጥሩ ዜጋ መሆን እንዲችሉ ማብቃት፣ በቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ክህሎትና ብቃት በመጠቀም ራሳቸውን ማሳደግ የሚችሉበት ዕውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ የደህንንት ትምህርት በመማር እንዲጠመቁ ማድረግና የመሳሰሉት ስራዎች የሚሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በየአጥቢያው ቁጥራቸው በየጊዜው እየጨመረ እየመጣ ይገኛል፡፡ በተለይም ብዙ ጊዜ ቲኖች ወደ ተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስለሚሄዱ በሚሄዱበት ስፍራ ሊገጥማቸው የሚችለውን ተግዳሮትና ችግር መቋቋም እንዲችሉ መርዳት ዋነኛው የቲን ቤተ ክርስቲያን መርህ ነው፡፡ ይህንንም አሰራር በመጠቀም እድሜአቸው ሲደርስ ለወጣት ቤተክርስቲያን ብቁ የሆነ ዜጋ ለማፍራት ይሰራል፡፡ እንዲሁም ቀድመው በተቋቋሙ ሶስት አጥቢያዎች የቲን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተ ሲሆን በነዚህ አጥቢያዎች ደግሞ የእረኛነት ቡድን አላቸው፡፡ ይህም ማለት ቀድመው የነበሩት ቲኖች አዲስ የሚመጣውን ቲን በመከታተል ይጸልዩላቸዋል፣ ይከታተሏቸዋል፣ ይመሩዋቸዋል፡፡ ዋናው የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ቲኖችን ከማንኛውም ጥፋት መጠበቅ ነው፡፡ እንደዚሁም ቲኖች በአንድ ዕድሜ ደረጃ ያሉት ብዙ ጊዜ ስለሚፈላለጉ የራሳቸው አገልጋዮች እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡

 

የሕጸናት የአገልግሎት ክፍል /Department/

በቤተ ክርስቲያናችን የሚመጡትን ህጻናትን በተመለከተ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጣቸው በተተከሉት አጥቢያዎች ሁሉ ከፍተኛ ኪራይ /ወጪ/ እየተከፈለላቸው የመማርያ ስፍራ ይዘጋጅላቸዋል፡፡ ህጻናት የምንላቸው እድሜአቸው እስከ አስራ ሶስት ዓመት ድረስ ያሉትን ነው፡፡ እሁድ ጥዋት /በአምልኮ ወቅት/ በእድሜ በመለየትና የተለያዩ መምህራን በመመደብ የወንጌል ትምህርትና ስልጠና እየተሰጣቸው እየተኮተኮቱና፣ እየተመከሩ በእግዚአብሔር ቤት እንዲያድጉ ይደርጋል፡፡ እንዲሁም በአምልኮ ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፣ መዝሙር እንዲያቀርቡ እየተደረገ ይበረታታሉ፡፡

 

 

2017-04-30T05:21:50+00:00