Loading Events
This event has passed.

የሁለት ወር የጾምና ፀሎት ጊዜ ጅማሬ ከ15 አመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ፓስተር ብርሃን ከፓስተር ሜርሲና ከሌሎች ወገኖች ጋር በመሆን የተጀመረው ነው። ያን ጊዜ ፓስተር ብርሃንና ፓስተር ሜርሲ ገና አልተጋቡም ነበረ። ይህ የጾምና ፀሎት ጊዜ በቤተ-ክርስቲያናችን ከተጀመረ ጀምሮ የእግዚአብሔርን እርዳታ ያየንበትና ትላልቅ ሚስጥራትን የተረዳንበት ሆኖአል። በአሁን ጊዜም በእያንዳንዱ አጥቢያ የሚደረግ ሲሆን በየአመቱ አዳዲስ ሀይልን የምንቀበልበትና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ የምንሻገርበት ነው።

የ2010 አመትም የጾምና ፀሎት ጊዜ መድረሱን በጣም በደስታና በአክብሮት በማሰብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት በአንድነት የምንሆንበትን ጊዜው አሁን ነው። በየአመቱ ከምናየው አዳዲስ የእግዚአብሔር ክብር የተነሳ መቼም ቢሆን ልንለምደው የማንፈልገው፣ የማንሰለቸውና በጉጉት የምንጠባበቀው ሰአት ነው። እግዚአብሔር ብዙ ፈውሶችን የሰጠን፣ የሕይወት ደረጃችንን የቀየረበት፣ የአገልግሎት ድንበራችንን ያሰፋበት፣ የቤተ-ክርስቲያን ራዕይ የተቀበልንበት፣ የአመራርና የአሰራር ጥበብ ያገኘንበት እና ብዙ መናን የተቀበልንበት ነው። በዚህ አመት ርዕሳችን መብዛት የሚል ነው። እግዚአብሔር እንደተናገረን የርኆቦት አመታችን ላይ እግዚአብሔር በሁሉ አቅጣጫ የሚያበዛን እና የሚያሰፋን ጊዜ ነው።


ቀን:

  • የ2010 አመት የጾምና ፀሎት ጊዜ ከየካቲት 5 እስከ መጋቢት 30 ይሆናል።

የአንድነት የፀሎት ሰዓት:

  • ቴሌኮንፍራንስ (አሜሪካ): ሰኞ – ቅዳሜ ጠዋት 12:00 – 1:00 ፣ ማታ 2:30 – 4:00 (ከዕሮብ ማታ በስተቀር)  (404-4100855) 
  • በቤተ-ክርስቲያን (አትላንታ): አርብ ማታ 2:30 – 7:00
  • በቤተ-ክርስቲያን (ኢትዮጵያ): ሰኞ – ቅዳሜ ጠዋት 3:00 – 6:30

አካሄድ:

  •  ምግብ፡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት በፊት የማይበላ ሲሆን እሁድ ለት ግን ከቀኑ ስድስት ሰኣት በኃላ መመገብ ይቻላል።
  •  የሚጠጣ፡ በፆም ጊዜ ብዙ ውሃን በመጠጣት መቆየት ይረዳል።

የየሳምንቱ ርዕስ:

  • እያንዳንዱ ሳምንት የራሱ የሆነ ርዕስ ሲኖረው በዚህ መሰረት በአንድ ልብ እና መንፈስ ሆነን ሁላችንም በያለንበት እንተጋለን።

መዝጊያ:

  • የአመቱ የሁለት ወር የፆምና ፀሎት ጊዜ የሚጠናቀቀው በእያንዳንዱ አጥቢያ በፋሲካ ሳምንት ሶስት ቀን ኮንፍራንስ በማድረግ ይሆናል።

The start of the annual two month prayer and fasting time dates back to 15 years ago when Pastor Birhan along with Pastor Mercy started to gather with few other friends. This was even before Pastor Birhan and Mercy got married. This heavenly tradition continued and became part of FGIC. For the years to follow, all FGIC local churches joined and this fasting and prayer time has become a strong force and backbone for where the church is today.

It is with great privilege and honor to come together once again for a new year to seek God during this time. There is always a new move of God and we never want to get used to it. We always expect greater and new things. We have experienced the hands of God every year after Fasting and Prayer. We have seen healing, restoration, new ideas, new vison and new strength over our church and those who join us for this time. This year, we are going to pray for MULTIPLICATION. It is our Year of Rehoboth and we shall Multiply in every direction.


DATES:

  • The 2018 annual two month Fasting and Prayer time will begin on February 12 and ends on April 8.

PRAYER TIMES:

  • Teleconference for USA: Monday – Saturday 6-7AM and 8:30 – 10PM (Except Wednesday evenings)  (404-4100855) 
  • Church Gathering (Atlanta): Fridays 8:30PM – 1AM
  • Church Gathering (Ethiopia): Monday – Saturday 9AM – 12:30PM

RULES OF CONDUCT:

  • Food: No food until 3 PM daily, except on Sunday. On Sundays, we fast until 12PM
  •  Drink: Please consume plenty of water throughout the day

WEEKLY ADENDA:

  • Each of the 8 weeks of fasting and prayer time will have its own prayer topic. We shall seek God and lead our congregation to pray with this same heart and spirit.

CONCLUSION:

  • The fasting and prayer time will conclude with three days conference at each church location