GO Office2017-07-04T15:55:12+00:00

GO Office
Called to Oversee

GO የሚለው ስም ሁለት ሀሳቦችን የያዘ ሲሆን የመጀመሪያው የበላይ ቢሮ (General Overseers Office) ወይንም በአጭሩ (GO Office) ሲሆን በዋናነት ደግሞ ሂዱ (Go) ብሎ እየሱስ ክርስቶስ በማቴ 28:19-20 ላይ ያዘዘንን የታላቁን ተልዕኮ ትእዛዝ የሚፈፅም ነው። ቢሮው በቤተ ክርስቲያኗ ራዕይ ተቀባይ በመጋቢ ብርሃን ጫነና በመጋቢ ሜርሲ መስፍን ሲመራ  የቤተ ክርስቲያኗ ዋና ተጠሪና ኃላፊ በመሆን በበላይነት ይሰራል፡፡ ይህም ማለት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ቤተ ክርስቲያኗን ይመራል፣ ያስተዳድራል፣ መመሪያዎችንና ደንቦችን ያወጣል፣ ያጸድቃል፣ አፈጻጸማቸውን ይቆጣጠራል፡፡  ከዚህ ቢሮ ስር 13 የቦርድ አባላት ሲኖሩት ይህ ቁጥር እንደአስፈላጊነቱ የሚጨምር ይሆናል፡፡ የእያንዳንዱ አጥቢያ  ቤ/ክ እና መሪዎች በሙሉ ተጠሪነታቸው ለዚህ ለቦርዱ ነው።

የዚህ ቢሮ ዋናው ግቡ በአስር ዓመት አንድ ሺ ቤተ ክርስቲያን መትከል የሚለውን ራዕይ ማስፈጸም ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ተከላ አገልግሎት አፈጻጸም ያመች ዘንድ በአስተባባሪ (coordinator) የሚመራ ፅህፈት ቤት የተቋቋመ ሲሆን በተመረጡ ስፍራዎች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትን በመትከል እየተንቀሳቀሰ ከበላይ ቢሮ በሚሰጠው የአተካከል መመሪያ መሰረት የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡ ይህ አገልግሎት አዲስ ለሚከፈቱ አጥቢያዎች ቦታዎችን ያፈላልጋል። በተገኘውም ቦታ ቤ/ክ ለመትከል የሚያስፈልገውን ስራ ማለትም ግንባታ ወይም እደሳን እና አስፈላጊ እቃዎችን ሁሉ መግዛት እንዲሁም ለስራው ከሚያስፈልጉ ባልደረቦች ጋር አብሮ በመስራት ተከላውን ያስፈጽማል። አጥቢያዎቹ ከተተከሉም በኋላ ሁኔታዎችን በቅርብ ሆኖ በመከታተል ለቤ/ክ መሳካትና መከናወን የሚያስፈልገውን እገዛ ያደርጋል።። በዚሁ የበላይ ቢሮ የሚመሩ ሌሎችም አገልግሎቶች የተቋቋሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል:-

  • የወንጌልና የክሩሴድ ዲፓርትመንት: ይህ ዲፓርትመንት የጀማ ስብከትን፣ ሁሉንም እድሜዎችን ያካተከ የተለያዩ ከተማ እና አገር አቀፍ የሆኑ የወንጌል ሥርጭቶችን እንዲሁም አዳዲስ አጥቢያዎች ከመከፈታቸው በፊት ቀድሞ በመሄድ በከተማው የወንጌል ሥራን በመስራትና አዳዲስ ነፍሳትን በማዳን ወደ ቤ/ክ እንዲመጡ ይሰራል።
  • የስነ-ጽሑፍ ዲፓርትመንት ደግሞ የሚታተሙ መፅሐፎቶችንንና መፅሔቶችን በማዘጋጀት ለቤ/ክ የማስተማሪያ እና የአመራር መተዳደሪያዎችን በፁሑፍ ያቀርባል። በመጋቢዎቻችን የተፃፈውንም “ትዳራችንን እንዴት እንፈወስ?” የሚለውን የመጀመሪያ እትም አዘጋጅቶ ለገበያ ያቀረበ ሲሆን አሁንም እትም ሁለትን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
  • የሚዲያናኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት የእግዚአብሄር ፍፁም ሙላት ቤ/ክ በራሷ ቴሌቭዥን እና ሬዲዮ ጣቢያዎች ላይ አገልግሎቷን አንድታስተላልፍ እና ቤ/ክ የማይመጡ ሠዎች ጋር ወደቤታቸው ለመድረስ ለምታደርገስ እንቅስቃሴ ሲሰራ፣ በተጨማሪም የተለያዩ በዘመኑ ያሉትን ማህበራዊ ደህረ-ገፅ አቅራቦቶችን በመጠቀም የእግዚአብሔር ስራ ለማስፋፋት ይተጋል። ከዚህም በተጨማሪ ኦዲዮ እና ቪዲዮን በማዘጋጀት እና በማሳተም እንዲሁም እ/ር በመሐከላችን እየሰራ ያለውን ሥራ በመቅረፅ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ እና እግዚአብሔር በቤክርስቲያናችን እያደረገና እየሰራ ያለውን ስራ እንድንመለከት ይረዳናል።

እያንዳንዱ ዲፓርትመን በሀላፊነት የተሾሙ መሪዎች ሲኖረው ስራው በታላቅ ክንውን እየተሰራ ይገኛል። በሁለት አመት ተኩል ውስጥ ዘጠኝ አጥቢያዎች የተተከሉ ሲሆን ይህም ማለት በሶስት ወር አንድ አጥቢያ እየተተከለ ነው ማለት ነው። ሁሉም አጥቢያም ቤ/ክ አሳድጋና  አሰልጥና በላከቻቸው የቤ/ክ ፍሬዎች የሚመሩ ናቸው። ይህ ከእግዚአብሔር ብቻ የሆነው ስራ የ1000ሺ ቤ/ክ ራዕያችንን ይዘን እስከምንፈፅም ድረስ ይቀጥላል።