Freedom Bible School2017-04-30T03:41:21+00:00

ይህ ት/ቤት መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን ማስተማር የጀመረው በላፍቶ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበር፡፡ ኤ.ቢ.ኢንፎ (A.B Info) የሚባለው ት/ቤት በነጻ በሰጠን የማስተማርያ ክፍሎች በመጠቀም ትምህርቱንና ስልጠናውን መስጠት ጀመርን፡፡ ሠዎችን አርነት ለማውጣትእግዚአብሔር ቃል ለማስተማር ተጀመረ።
የእግዚአብሔር ቃል፣ መንፈስ ቅዱስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናጥና፣ ጥበብን በሚመለከት፣ የጋብቻን ሕይወት በሚመለከት፣ ወንጌልን እንዴት እናሰራጭ በሚልና እነዚህን በመሳሰሉ በዋና መሪዎቻችንና ከቤተ ክርስቲያኖቻችን ውጪ በአሉ አገልጋዮችን መሠረታዊ እና ተግባራዊ የሆኑ መፅሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን የሚሰጥ ነው።
ይህ ት/ቤት በላፍቶ ከሚገኘው ከዋናው ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ በአጥቢያ ደረጃ በአለም ገናም ተጀምሯል፡፡ ለወደፊት በእያንዳንዱ አጥቢያ ቅርንጫፍ ይኖረዋል፡፡ ለዚሁ ት/ቤት አስተማሪነት ሲባል በሀገሪቱዋ እና በውጭ አገር ባሉ በቲዎሎጂ ኮሌጆች ከሃያ የሚበልጡ በዲፕሎምና በዲግሪ እንዲመረቁ ከማድረጋችንም በላይ በማስተሬትና በፒ.ኤች.ዲ ደረጃ እንዲማሩና ለማስተማር ብቁ እነዲሆኑ እያደረግን እንገኛለን፡፡
ይህ ት/ቤት ሙሉ በሙሉ ሲደራጅ በዲፐሎማ፣ በዲግሪ፣ በማስትሬት ማስመረቅ የምንችልበትን ሥራ በመሥራት ላይ እንገኛለን፡፡ ስልጠናውም በተለያዩ ቋንቋዎች ይሆናል ማለት ነው፡፡
ዓላማችን ይህ ት/ቤት አድጎ የራሱ አመራርና አስተዳደር እንዲኖረው ተደርጎ በበላይ ቢሮ (Go Office) ስር እየተዳደረ እንዲሰራ ይደረጋል፡፡ በቤተክርስቲያናችን ትልቅ ጠቀሜታ የሚኖረውና ትልቅ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብለን የምናስበው ት/ ቤት ነው፡፡ እንደውም ይህ ት/ቤት በእድገት ወደ አዳሪ ት/ቤት ብንቀይረው ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለን አምነናል።
ተግባራዊ የሆነና በደንብ የተደራጀ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ ያለው ት/ቤት ይሆናል ፡፡ ስለ መንፈስ ቅዱስ አስተምሮ መንፈስ ቅዱስን የሚለማመድ፣ ወንጌልን አስተምሮ ወንጌልን ስብከትን የሚለማመድ፣ ፈውስን አስተምሮ ፈውስን የሚለማመድ፣ ስለ አመራር አስተምሮ አመራርን የሚለማመድ ት/ቤት ይሆናል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት መድረስ ያለ አውቀትና ትምህርት እንደማይቻል እናምናለን፡፡