Antioch Missionary School

የአንጾኪያ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት የተመሰረተው ቤ/ክ ለመትከል የሚላኩ አገልጋዮችን ለማሰልጠን ነው። በ2007 (2014) ተቋቁሞ በጣም ውጤታማ የሆኑ ቤተ ክርስቲያንን የተከሉ ሰዎችን ያበቃ ት/ቤት ነው፡፡ ይህንን ስያሜ እንዴት አገኘ ካልን በመፅሀፍ ቅዱስየአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳን ከኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ቀጥላ የተቋቋመች ብትሆንም የምትልክ ቤተ ክርስቲያን ነበረች ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተወሰደ ነው (ሐዋ 13:1-2)፡፡ ይህቺ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ድምጽ ዻውሎስንና በርናባስን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ ሲል ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያኗ ወሳኝ ሰዎችና መሪዎቻቸውም ቢሆኑም እነርሱን የላከች ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ እንዲሁም የዚህች ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በፈቃደኝነት የወጡ ነበሩ፡፡ ሚሽን ተኮር የሆኑ፣ ዋጋ ሚያስከፍሉ ሁኔታዎችን እና ያልተደፈሩ አካባቢዎችን የሚደፍሩ ጀግና ተላኪዎችን የምታዘጋጅና የምታበቃ ከተላኩም በኋላ የምታስተምር ት/ቤት ናት፡፡

2017-04-30T06:04:54+00:00